ዶ/ር ዘለዓለም እሸቴ ይመር
የሚከተለው ውጤት ድህረ ገፆች ላይ ከወጡት ፅሁፎቼ ሊንክ በማድረግ በ www.myEthiopia.com ድህረ ገፅ ላይ የተሰበሰበ የዳሰሳ ጥናት ነው። ጥናቱ ሳይንሳዊ ያልሆነ ቢሆንም ለመንደርደሪያ ጥናትና አሳብ ሊረዳ ይችል ይሆናል ብዬ አስባለው። ይህ ማለት ስለ እርቅና መግባባት ውስብስብ ጥያቄ እልባት ለማግኘት አይደለም። ያ በእኔ አይሞከርም ከአቅሜ በላይ ነውና። ዓላማዬ ስለ እርቅ ቅድመ ሁኔታዎች መንደርደሪያ አሳብ ለመሰብሰብ በማሰብ ነው። እነሆ ድምፅ የሰጡትን ሰዎች አሳቦች አጠርና ጠቅለል አድርጌ ከዚህ በታች በጥሬው አቅርቤያለው። የራሴን ትንታኔ ትቸዋለሁ። ያንን ለአንባቢው እተዋለሁ። በዚህ ዳሰሳ ጥናት ላይ የተሳተፉትን ከልብ አመሰግናለው። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ። ፍቅርም ይስጠን።

Q1: Which generation are you? የትኛው ትውልድ ነዎት?
77.5% I am 30 years old or above ሰላሳና ከሰላሳ አመት በላይ ነኝ
22.5% I am less than 30 years old ከሰላሳ አመት በታች ነኝ
Q2: Reconciliation is the only way out for Ethiopia? እርቅና መግባባት ብቸኛ መፍትኤ አድርገን መውሰድ ይገባናል?
86% Agree እስማማለሁ
14% Disagree አልስማማም
Please tell us if you have other ideas (ተጨማሪ አዲስ አሳብ ካለዎት ይንገሩን) (ዝርዝሩ ከታች ይቀጥላል)
Q3: Who should reach out for reconciliation first? ለእርቅና መግባባት ቀደምተኛውን በጎ ድርጊት ማን ይጀምር?
48.5% Government መንግስት
21.5% Ethiopian elders የአገር ሽማግሌዎች
21.25% Other Option ሌላ (ዝርዝሩ ከታች ይቀጥላል)
8.75% Opposition ተቃዋሚ
Q4: Who has a solution for Ethiopia’s complex problems? ለኢትዮጵያ ውስብስብ ችግር ማን መፍትኤ ያመጣል?
69% Both reconciled ሁለቱም በእርቅ
17.75% Other Option ሌላ (ዝርዝሩ ከታች ይቀጥላል)
6.75% Government መንግስት
6.5% Opposition ተቃዋሚ
Q5: Ask God’s blessings on a national level (like USA) በብሔራዊ ደረጃ የአምላክን በረከት እንጠይቅ (እንደ አሜሪካ)
83% Agree እስማማለሁ
17% Disagree አልስማማም
Total Complete Responses = 400 (ጠቅላላ የተሟላ ድምፅ)
Q2: Reconciliation is the only way out for Ethiopia? Please tell us if you have other ideas (እርቅና መግባባት ብቸኛ መፍትኤ አድርገን መውሰድ ይገባናል? ተጨማሪ አዲስ አሳብ ካለዎት ይንገሩን።
Q3: Who should reach out for reconciliation first? (OTHER responses) (ለእርቅና መግባባት ቀደምተኛውን በጎ ድርጊት ማን ይጀምር? ሌላ አሳብ የተሰጠ •••
Q4: Who has a solution for Ethiopia’s complex problems? (Other Option) (ለኢትዮጵያ ውስብስብ ችግር ማን መፍትሔ ያመጣል? ሌላ አሳብ የተሰጠ •••

- መንግስት ስህተቱን አምኖ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ መጠየቅ
- የአይል ሚዛን እኩል እስኪሆን እርቅ አሁን አያስፈልግም
- አንድ ላይ እንሁንና ያለፈውን ቂም እንርሳና በሰላም አብሮ በመኖር ኢትዮጵያን እናሳድግ
- ማንና ማን ይታረቅ? የፖለቲካ ፓርቲዎች ወይስ ዘርና ጎሳ? የትኛው ይቅደም?
- ከእርቅ ውጭ ሰው ሰራሽ ከሆነው ውስብስብ ችግር የሚታደገን መፍትኤ የለም
- የሰላሙ ትግል ባገር ውስጥም ሆነ በኢንተርናሽናል ይጨምርና በመንግስት ላይ ጫና ካላደረገ እርቅ አይሰራም
- እርቅና መግባባት የተባረከና ለሕዝባችንና ለተወዳጁ አገራችን አንድ እምርታ ነው
- ቅድመ ሁኔታ የሚያስቀምጡ ካሉ እንዴት ሊሆን ነው?
- አመፅን የሚያራምዱ የእርቅ እንቅፋት እንዳይሆኑ ምን ማድረግ ይቻላል?
- እርቁ ዘላቂ መፍትኤ እንዲኖረው ሰነድና አስፈፃሚ ህግ ሊኖረው አይገባምን?
- እርቁ ስልጣን ለማግኘት መሆን የለበትም። ይልቁንስ ባረጀው ትውልድ መተማመንን ለመፍጠር ይሁን
- በመጀመሪያ መከባበር አለብን
- በቃላት ብቻ ሳይሆን በስራ እንዋደድ
- ይህ መንግስት እርቅና ሰላምን እሺ አይልም። እርቅ አይሰራም።
- በኢትዮጵያ ጦርነትን ማየት አልፈልግም
- እርቅ ማለት በሃይማኖት መቻቻል መፍጠርን ያጠቃልል።
- የበደለ አምኖና ስህተቱን ተቀብሎ ይቅርታ መጠየቅ አለበት
- ኢትዮጵያዊነትን እንደገና በአዲስ መልክ መተርጎም ያስፈልጋል።
- እርቅ ማለት ያለፈውን ስህተት ማስተካከል ይጠይቃል።
- ከኢአደግ ጋር ብቻ ሳይሆን ካለፉት መንግስታትም ጭምር እርቅ ያስፈልጋል
- እርቅ ፍትሕን ይጋፋል፥ የበለጠም በዳዩን ይጠቅማል
- እርቁ በሁለቱም በኩል ያለ ሃይል በፈቃደኝነት ተቀባይነትን ማግኘት አለበት
- በእውነት ስለ እውነት መነሳሳት ይገባናል
- መንግስት እልህኛ ከመሆን ቶሎ በጠረጴዛ ዙሪያ እንሰብሰብና አባይም ይገደብ
- ኢትዮጵያን ከወደድን ህዝቡን እንውደድ፥ ድግሞም የምንጠላውንም ሰው እንውደድ
- ልዮነታችን ብቻ ሳይሆን ጣልቃ የምናስገባውም ነገር መቅረት አለብን
- ቅን ልቦና ከሌለ እርቅና መግባባት አይሰራም
- ለእኛ አገር ከእርቅና መግባባት የሚቀድም ነገር የለም
- የታሰሩት ሁሉ መጀመሪያ እንዲፈቱ ይሁን (ምህረትም ተደርጎ ቢሆንም)
- ስልጣን የሕዝብ ብቻ መሆኑንና መንግስትም የሚወክለው ህዝብን ብቻ መሆኑን ሁሉም ይመን
- ችግራችንን እኛው ራሳችን እንፍታ
- በእሳት ላይ ጋዝ ሳይሆን ውሃ የሚጨምር ትውልድ ያስፈልገናል
- ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ መፍትት እየተቻለ በብጥብጥና በጥላቻ ለመፍታት መሞከር ሞኝነት ነው
- ሞተን ሁሉን ትተን ለምንሄደው መልካምን ስም ትተን እንለፍ
- እርቅ እንዲሰምር በህብረተሰባችን ውስጥ ያለፈውን ፍትሕ አልባ ሁኔታ እንደገና ዛሬም ለመመለስ አይሞከር
- እርቅ ብቸኛ ምርጫችን ነው
- እርቅና መግባባት ከማንና ስለ ምን ጉዳይ ነው?
- አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የትምህርትና የንቃተ ህሊና ደረጃ ለዚህ መልስ ለመስጠት አልደረሰም
- ላለመስማማትም እየተስማማን የሁላችንም የሆነችው ኢትዮጵያ ናት
- በጎ አሳብ ቢሆንም የሚሆን አይመስልም። ግን እፀልያለው እንዲሆን።
- አማራው ለሁሉ ነገር ኢአዴግን መውቀስ ትቶ ያለፉት አማራ ገዥዎች ያደረጉትን ይመርምሩ
- ከድህነት መውጣት ብቸኛው መፍትኤ ነው
- እርቅና መግባባት ብቸኛውና ድንቁ መንገድ ነው
- ኢአዴግ እሺ አይልም። ይህ ከህልም ያለፈ አይደለም
- ያለፈው ታሪካችን ጥሩም ሆነ ክፉ እንማርበት እንጂ ለመጣላት ምክንያት አይሁንብን
- ከእርቅ በፊት መረጃ ፕሮፖጋንዳን ይተካ፥ አገሪቱ እውነትን በመክዳት ላይ ነች ያለችው
- አገዛዙንም ሆነ ታጣቂዎችን ተቀምጠው እንዲደራደሩ የሚያስገድድ ሃይል ያስፈልጋል
- እርቅ ማለት ምን ማለት ነው? ጥፋተኛን ወደ ፍርድ ማምጣት አይጠቀልልም?
- እርቅ ላለፉት 150 በላይ አመታት አማራና ትግሬ ያደረገውን ስህተት ይቅርታ በመጠየቅ ይጀምር
- ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በአዲስ ትውልድ ከሁሉም ለሁሉም አሳታፊ የሆነ ቢሆን ከቂመኝነት ይፀዳል
- እርቅን በመጀመሪያ ከራስ ጋር ይጀምር። ያኔ ሁሉም ይቀላል።
- እርቅ የትግሉን መስክ እንዳያዘናጋ እንጠንቀቅ
- ለነፃነት እንዋጋ
- ጥላቻን እስወግደን፥ መሃከለኛው መንገድ መፍትኤ ነው
- አንድነትን ካልፈጠርንና ልዩነታችንን ካላቻቻልን፥ ኢትዮጵያ ለሚቀጥለው ትውልድ አትተላለፍም
- እርቅ መልካም ነው ግን ምን ይቅር እንደሚባል መጀመሪያ መስማማት አለብን።
- እርቅ ይሁን ግን ሕግን የተላለፉት ተጠያቂ ይሆኑ ዘንድ ይገባል። ወደ ፍርድ መምጣት አለባቸው።
- ዝም ብለን ከተቀመጥንና ለችግራችን መፍትኤ ካልፈለግን ኢትዮጵያ ወደ እርስ በርስ ጦርነትና ብጥብጥ ታመራለች
- እርቅን በፍፁም አንፈልግም።
- በመጀመሪያ የዘር ጉዳይ ይታይ። ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል ነው።
- መንግስት ያደረገው መልካም ነገር ምስጋና ይሰጠው።
- እርቅ በተቃዋሚዎች መካከል ያስፈልጋል
- ዲሞክራሳያዊ መዋቅሮች፥ የህግ የበላይነት፥ ነፃና ፍታዊ ምርጫና ነፃ ፕሬስ ሰላም ያመጣል።
- በእርቅና መግባባት የሚያምኑ ሁሉ የጋራ መድረክ ፈጥረው አሳቡን ያዳብሩ
- የበላይነት ወይም የበታችነት ስሜት ይቅር
- የዘር ክፍፍልና ጥላቻን ለመፈወስ የሚያስፈልገው እርቅና መግባባት ነው
- እርቅ ብቸኛ ምርጫ ሊሆን አይገባም።
Q3: Who should reach out for reconciliation first? (OTHER responses) (ለእርቅና መግባባት ቀደምተኛውን በጎ ድርጊት ማን ይጀምር? ሌላ አሳብ የተሰጠ •••
- ይህ መንግስት ከወረደ በዋላ እንደ ደቡብ አፍሪካ ይሁን
- ዜጎቹን ለማሰባሰብና ለሃገሪቱ ሰላም ለማምጣት ሃይልና ሃላፊነት ያለው መንግስት ነውና መንግስት ይሁን
- እያንዳንዳንዱ ሰው
- ሽማግሌም ባይሆን ግን በህዝቡ ተሃማኒ የሆነ ቅንና ገለልተኛ በእውነትም ኢትዮጵያን የሚወድ ሰው ይሁን
- የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ
- ተቃዋሚው በአንድነት ተደራጅቶና የተቀናጀ ፕሮፖዛል ለህዝብ ያቅርብና ብሔራዊ ቀን ይጥራ
- መንግስት ተቃዋሚ አለኝ ካለ የሚቃወሙት ምንድነው? ብሎ መጋበዝ አለበት
- የተዘረዘሩት ምርጫዎች ሁሉ ያካተተ ይሁን
- አንድ ሰው (ማን ይሁን ኢትዮጵያዊ ማንዴላ)
- ሁለቱም ስምምነቱን ገለልተኛ ሶስተኛ አካል ባለበት ይፈራረሙ
- እርቅ አያስፈልግም። ዲሞክራሲ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ስምምነት ይኑረን ብቻ
- የኢትዮጵያ አባወራ መንግስት ነውና የመጀመሪያውን የእርቅ በር መንግስት እንደ አባት ይክፈትና ይጀምር
- መንግስትና ተቃዋሚ በአንድነት ይጀምሩ
- እርቅና መግባባት የሚጠቅማቸው ሁሉ እኩል ሃላፊነቱን ይውሰዱ
- መንፈሳዊ መሪዎች፥ ግን ተጠሪነታቸው ለአምላክና ለህዝቡ ብቻ የሆነ
- ከሁሉም ጎሳዎች በዲሞክራሲ አመራረጥ የተመረጡ ሽማግሌዎች (ሁሉንም ብሔር የሚወክሉ)
- የመንግስት ቁርጠኝነት ለእርቀ ሰላሙ መሳካት ጉልህ ሚና አለው
- ማንም ቢጀምር መንግስት በቀና ልብ ካላየው ፍሬያማ አይሆንም
- መንግስት ተቃዋሚና ሽማግሌዎች አብረው
- ሁሉም ሃላፊነት አለው፥ ግን መንግስት ይስማማ በአሳቡ
- የሚያስከፍለውን ዋጋ ከፍሎ
- የሚቀጥለው ምርጫ ፍታዊ ክሆነ በዋላ
- ከህፃናት በስተቀር በህይወት ያለ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሲተባብር ብቻ ነው የሚሳካው
- ከራስ ይጀምራል
- ከመንግስት ይልቅ እርስ በርሱ የተጣላው ተቃዋሚው ክፍል ነው
- መንግስት በእርቅ ላይ የሌለውን ጊዜ አያባክን
- ከውጭ አገር ከምንኮርጅ፥ በራሳችን ባህል እርቅን እናውርድ፥ ሽማግሌዎች ይምሩን
- ስልጣን ቢሞት የማይለቅ መንግስትና ራዕይ የሌለው ደካማ ተቃዋሚ ስላለን መፍትኤ የለም
- ምሁራን፥ የሃይማኖት መሪዎች፥ ተፎካካሪና የመንግስት ተወካዮች፥ በፖለቲካ ያልተሳተፉ ሁሉ በጋራ
- ሽማግሌዎችና አባቶች ይጀምሩ
- አማራ ያለፉትን ጨካኝ አማራ መሪዎችን መደገፍ ያቁሙ
- ነፃ የሆነ ከመንግስት፥ ተቃዋሚና ሽማግሌዎች የተውጣጣ ካዉንስል
- ኢትዮጵያውያን የሆኑ የስብሃዊ መብት ታጋዮች፥ ሃይማኖታዊ መሪዎችና ሲቪል ተቋማት
- መንግስት መጀመሪያ ይቅርታ ይጠይቅ
- ከታች የሕዝብ ንቅናቄ
- በመካከል ሆነው መንግስንና ተቃዋሚን የሚደግፉ
- ከመንግስት በስተቀር ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች ሊጀምሩ ይችላሉ
- የድሮ ፓርቲዎች እርስ በርሳቸው ሰላም ይፍጠሩና ከፖለቲካ ራሳቸውን ያግልሉና አዲሱ ትውልድ ይረከብ
- ሶስተኛ ነፃ አካል (ከአሜሪካና ከእንግሊዝ ውጭ) በዚህ ላይ ይሳተፉ
- የተከበሩ ሽማግሌዎች ከተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች የተውጣጡ
- መጀመሪያ እርቅ በተቃዋሚዎች መካከል ይሁን
- ሁሉም ሃይማኖቶችና የዘርና ጎሳ ክፍሎች
- ተቃዋሚዎች ይጀምሩ (ምሁራንና ግለስቦችን ይጨምርና)
- ከፖለቲካ ነፃ የሆነ ማንኛውም ተቋምና ድርጅት መጀመር ይችላል
Q4: Who has a solution for Ethiopia’s complex problems? (Other Option) (ለኢትዮጵያ ውስብስብ ችግር ማን መፍትሔ ያመጣል? ሌላ አሳብ የተሰጠ •••
- ህብረተሰቡ
- ሰላም መፍጠርና ነፃ ምርጫ መፍትሔ ያመጣል። መጀመሪያ የአገሪቱ ሰራዊት የህዝብ መሆን አለበት።
- የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ፥ በተለይ ወጣቱ ትውልድ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ አለበት
- እግዚሆ እንበል
- የውጭ ረጅ ድርጅቶች በነገሩ ላይ ይሳተፉ
- ወጣቱና ሴቶችን ያሰባሰበ መግባባት በቤተሰብ ደረጃ ሲጀምር፥ ከዚያም በጎረቤት እያለ ለውጥ ይመጣል
- ነፃ የህዝብ ተወካዮች፥ መንግስትና ተቃዋሚዎች
- ሁሉም መንግስት ተቃዋሚና እያንዳንዱ ዜጋ
- ሁሉም ዜጋ (በፖለቲካ የሚሳተፉ ብቻ አይደሉም)
- መንግስት ብዙ የተከፋፈለ ተቃዋሚ ይፈልጋል፥ ይህ ችግር ነው።
- አንድ ወጥ አገር ሳይሆን ልዩነታችንን እንከባከበው
- ምሁራን በመጀመሪያ እርስ በርስ ለስልጣን ከመጣላት እንደ ጋና ምሁራን ጥሩ ሚና ይጫወቱ
- ሁሉም ስልጣንን ብቻ ዓላማ አድርጎ መንቀሳቀስ ሲያቆም
- ሁሉም ያለው በመንግስት እጅ ነው
- ከመቶ በላይ የሆኑትን ፓርቲዎች ወደ ሁለት በመቀየር (ብሔራዊና ጎሳዊ)
- በጎ ህሊና ያለው በሙሉ፥ ሁሌም ፈጣሪ ያግዘናል
- ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ነው መፍትሔው (ታይዋን ሲንጋፖር ሆንክ ኮንግን ተመልከቱ)
- ሴቶች፥ ወጣቶች በማናቸውም ፖለቲካን ዘር ጎሳ ጥቅማጥቅም ያልተለከፉትን ማፈላለግና ማሰባሰብ
- የጥላቻ ፖለቲካ መፍትሔ አያመጣም ብለው የሚያምኑ ሁሉ
- ከየጎሳው የተውጣጡና ኢትዮጵያን የሚወክሉ ሁሉ
- ዋናው መንግስት ሲሆን ባነሰ መልኩ ተቃዋሚ
- እግዚአብሔር
- ህዝቡ ነው እንጂ መንግስትና ተቃዋሚ አይደለም
- መንግስት እሺ አይልምና የገበሬው አብዮት
- ተቃዋሚና ሕዝቡ
- በመንግስትና ተቃዋሚ እርቅ ቢፈጠርም የኢትዮጵያን ስር የሰደደ ችግር አይፈታም
- ሁሉም በእርቅ የሚወልዱት አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ
- እርቅ ይቻላል ብለው የሚያምኑት ሁሉ
- የድሮ የግፍ ኢትዮጵያ ለማምጣት የሚታገሉና የአሁኗ የጎሳ ኢትዮጵያን የሚያቀነቅኑ መሃከል ያለው ሽኩቻ ሲፈታ
- ሃይማኖት አለመንካት
- ነፃነትና ዲሞክራሲ
- የተደባለቀ ጎሳ የተወለዱ